1 020подписчиков сейчас
Публикации всего: 25
መልአክትም ምህረትን ስለ ሰው ልጅ ይጠይቃሉ
✅ዘካርያስ 1:12፤ የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ “አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ። ✅እና ዘወትር በአምላካችን እግዚኣብሔር ፊት የሚቆሙ መልእክት የኛ መልአክቶች ናቸው
🔰ማቴዎስ 18:10፤ “ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። 🔰እናም የቅዱሳንን ፀሎት ደግሞ ከእጃቸው በእግዚአብሄር ፊት ይወጣል ✅ ራእይ 8:4፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ። 🔰እናም መላእክትም በምድር ላይ የሚከናወነውን ያውቃሉ ✅ ሉቃስ 15:10፤ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።” ✅✅ስለዚህም በመላእክትና በቅዱሳን አገልግሎት መጠቀም ለኛ ትልቅ ጥቅም ነው
✅ዕብራውያን 1:13፤ ነገር ግን ከመላእክት፦ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፡” ከቶ ለማን ብሎአል?
14፤ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?
23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። 🔰በዚም በዛም የሚሰራው የጌታ ፀጋና ሀይል ነው ጌታ የተለያዪ ብልቶች አድርጎ ይሰራል
ምልጃ ማለት በልመና ሰዎችን ማስታረቅ ሲሆን አንዱ ስለ ላላው መለመን ወይም መፀለይ ምልጃ ይባላል ማስታረቅ በምልጃ ወይም በቤዛነት ሊሆን ይችላል ለምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ቤዛችን የበደላችንን ዋጋ ሁሉ የከፈለልን አምላካችን ነው እሱ ባስታረቀን ማስታረቅ ማንም ሊያስታርቀን አይችልም ምክኒያቱም ከታችን ከውድቀታችን የምንነሳበት ፀጋችን ሀይላችን ክፍያችንም ስለሆነ
✅ዕብራውያን 1:3፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ✅ 1 ቆሮንቶስ 1:30-31፤ ነገር ግን፦ “የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ፡” ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
✅ ኤፌሶን 1:7፤ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
✅ 1 ጢሞቴዎስ 2:5፤ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
6፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ 🔰ስለዜ ጌታ የፅድቃችን መሰለት የበደላችን ሁሉ መካሻ የሀጢያታችን ስርየት ወደ እግዚኣብሔር መድረሻ እርሱ ግንድ ሆኖ እኛን ደግሞ የእርሱ ቅርንጫፍ የሚያደርገን በራችን ጌታችን መድሀኒታችንም ነው ነው ♦️ምልጃ ደግሞ አንዱ ስለሊላው መለመን ወይም መፀለይ ሲሆን ይህን ማንም በጌታችን ግንድነት ላይ ቅርንጫፍነቱ የሆነለት ሰው ሊያደርገው ይችላል
✅ 2 ቆሮንቶስ 9:14፤ ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል። 🔰ምልጃ ደግሞ እግዚኣብሔርን የሚያስደስት ነው
✅1 ጢሞቴዎስ 2:1-2፤ እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።
3-4፤ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 🔰እኛ ደግሞ ክርስቲያኖች እርስ በራሳችን አንድ አካል ላይ እንዳሉ ብልቶች እንተሳሰባለን ✅ 1 ቆሮንቶስ 12:18፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል።
19፤ ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
20፤ ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው።
21፤ ዓይን እጅን፦ “አታስፈልገኝም፡” ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን፦ “አታስፈልጉኝም፡” ሊላቸው አይችልም። 🔰እነዚህ አካላት ውስጥ ደግሞ ብዙ ብልቶች አሉ ለምሳሌ
ዕብራውያን 12:22፤ ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
23፤ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ 🔰ስለዚህ እኛ እንደ አንድ አካል ስለሆንን በእግዚአብሄር ፊት እንተጋገዛለን አንዱ ሌላውን ያግዛል ✅ 1 ቆሮንቶስ 12:26፤ አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
27፤ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።
🔰እናም ግን የቅዱሳን ምልጃ ከኛ የሚየው እና እነሱን የበለጠ ለምልጃ የምንጠይቀው የነሱ ፀሎት ሀይል ስላለው ነው ለምሳሌ
✅ያዕቆብ 5:17፤ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
18፤ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። 🔰የኤልያስ ፀሎት ሰማይ ዝናብ እንዲሰጥ እና እንዳይሰጥ ሲያደርግ ነበር። የኛስ ፀሎት??? እኛስ በፀሎታችን ምን አድርገናል?? ለዛም ነው በጠንካራዎቹ አካሎቻችን ከፈጣሪ ስንጠይቅ እነሱ ደግሞ ያማልዱናል 🔰ታዲያ ሁሉ ቦታ ይገኛሉ ከተባለ ሁሉ ቦታ ስለሚገኙ ሳይሆን አንድ ቦታ ሆነው ግን መስማት ይችላሉ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሀንስ ምድር ላይ አንድ ቦታ ሆኖ ✅ ራእይ 5:13፤ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፡” ሲሉ ሰማሁ። 🔰እንዲሁም አብርሀም በስጋ በሂወት ሳይኖር በምድር ላይ የሚካሄደውን ያውቅ ነበር
✅ ሉቃስ 16:27፤ “እርሱም፦ ‘እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤
28፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው፡’ አለ።
29፤ አብርሃም ግን፦ ‘ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ፡’ አለው። 🔰ስለዚህ ይህ ፀጋ ለፃድቃን መንፈሶች የሚሰጥ ነው 🔰ቅዱስ ጳውሎስም በምድር ላይ ሳለ እንዲ ብሎአል
✅1 ቆሮንቶስ 5:3-4፤ እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ ✅✅✅ስለዚህ ምልጃ አንዱ ስለሌላው መለመን ሲሆን የቅዱሳኑ ግን በቃል ኪዳናቸው መሰረት ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ ስም የተሰጣቸው እግዚኣብሔር በቤቱ ከፍ ያለ ስም ሰጥቶአቸዋል የነሱ ምልጃ ደግሞ ሀይል ያደርጋል
✅ ኢሳይያስ 56:4፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦
5፤ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።
🔰🔰🔰🔰 እና ግን ጌታ ይሰማናል አይደለል እንዴ በራሳችን ብንፀልይ ለሚለው ደግሞ አው ጌታ ይሰማናል ግን እስኪ 1 ጥያቄ ከታች ያለው ጥቅስ ላይ
✅ያዕቆብ 5:14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
15፤ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። 🔰ስለ ቤተ-ክርስትያን ሽማግሌ ፀሎት ለምን ሀጢያት ይሰረይልናል??? 🔰ለምንስ ያ ሰው የቤተክርስትያን ሽማግሌ በሚጠራበት ቀጥታ ወደ ጌታ አልፀለየም ጌታ የልብን እንኩአን ያውቅ የለ
🔰🔰🔰🔰ሌላ ጥያቄ አምላካችን ኢየሱስ ለሀዋርያት ለምን ሀጢያት ይቅር የማለትና የመያዝ ስልጣን ሰጣቸው???
✅ዮሐንስ 20:22፤ ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።
23፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፡” አላቸው። 🔰🔰🔰መልሱ ቤተ-ክርስትያን የክርስቶስ አካል እንጂ ከክርስቶስ አካል ውጪ ስላልሆነች ✅ ኤፌሶን 1:22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።
ጌታችን የሞተው ስለ ስጋችን ወይስ ስለ ነብሳችን???
🟥ሀጥያት ለቤተክርስትያን አባቶች ለምን እንናዘዛለን??
መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል ለቤተክርስትያን የሰጣት ስልጣንስ በትንሹ ምን ይመስላል????
💠 ቤተ ክርስትያን የእውነት ሁሉ መገኛ ነች
1ኛ ጢሞቴዎስ 3
15፤ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
💠ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ አካል ክርስቶስም የቤተ ክርስትያን ራስ ነው
ወደ ኤፌሶን 1
22፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።
23፤ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።
💠💠 በቤተ ክርስትያን ያሉ ቅዱሳን ሁሉ ደግሞ የክርስቶስ ቤልቶች ናቸው
1ኛ ቆሮንቶስ 12
27፤ እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።
🟥🟥🟥 ስለዚህም ክርስቶስ አካሉ በሆነች ቤተ ክርስትያን ውስጥ አካል በመሆን የሚገለግሉ ቅዱሳንን ስራውን ይሰራባቸዋል
🔹 ዛሬ ስለ ሀጥያት ስርየት ስልጣን እንዴት አካሉን እንደሚጠቀም እንይ
🟢🟢 1ኛ ዮሐንስ 1
8፤ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
9፤ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
🔸🔸 ስለዚህ ሀጥያታችንን ስንናዘዝ ከሀጥያት በደሙ እንደሚያጦበን ይነግረናል ሀጥያትን ደግሞ ሰው ለሰው መናዘዝ እንዳለበት መፅሀፍ እንዲህ ይላል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
15፤ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።
16፤ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።
🟢🟢 በተጨማሪም ክርስቶስ አካሉ ለሆኑ ቅዱሳን የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጥቶ የማሰርና የመፍታት ስልጣን ሰጥተአል
የማቴዎስ ወንጌል 16
19፤ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
🟢🟢🟢 ይህንንም በማያወላዳ መልኩ ስለ ሀጥያት ስርየት ለሀዋርያት የተሰጠ ስልጣን መሆኑን ይናገራል 👇🏼
የዮሐንስ ወንጌል 20
23፤ ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፡ አላቸው።
🟢🟢ለዚ ነው በሀዋርያዊ ቅብብሎሽ በመልእክት ብቻ ሳይሆን በቃልም ሀዋርያትን እና የነሱን አምላክ ክርስቶስን አስተምሮ ተቀብላ 2ኛ ተሰሎንቄ 2
15፤ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።
የእውነት ሁሉ አምድና መገኛ የሆነችው ቤተ ክርስትያናችን ሀጥያትን ስለ መናዘዝ የምታስተምረው ለዚህ ነው🙏🏾🙏🏾🙏🏾
🟥🟢ብዙ ጥቅሞችም አሉት በመጀመርያ
1ኛ ዮሐንስ 4
20፤ ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥ እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
ይህን ቃል ወስደን እኛ በሰው ፊት የማናደርገውን በእግዚአብሄር ፊት ደግሞ ለመስራት ደፍረናልና ለሰዎች ስንናገር ሀጥያቱን ድጋሚ ላለመስራት እንሞክራለን ከሰራን ግን እግዚአብሄርን ፈርተን የግድ ለሰዎች መናዘዝ ስላለብን ሀጥያትን የመለማመድ እድላችን ይቀንሳል።
💠ሌላው ደግሞ ከሀጥያት እንዴት መመለስ እንዳለብን ምክር እናገኛለን
💠 ፀሎትን ስለኛ ያደርጉልናል በፀሎት ያግዙናል
የያዕቆብ መልእክት 5
14፤ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት።
💠💠 ወደ ሀጥያት እንዳንመለስ ሰይጣንን የምናሸንፍበትን መሳርያ (ፆም እና ፀሎት) ያስታጥቁናል
የማቴዎስ ወንጌል 17
21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፡ አላቸው።
💠💠🔸 የፃፍኩት ጌታዬና መዳኒቴ ክርስቶስ ኢየሱስ በረዳኝ ልክ ነው ምናልባትም የኔ ደካማነት ጌታ ከዚ በላይ እኔን እንዳይጠቀም አድርጎም ይሆናል🙏🏾🙏🏾🙏🏾🙏🏾
ግልፅ ያልሆነ ነገር ኬለ ጠይቁ 👉🏼 @ermi_hd
2ኛ ቆሮንቶስ 9
15፤ ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። 🟥በ @ermi_hd የተሰጠ መልስ
🛑ስእለ አድኖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነውን? ኪሩብ ማለት እኮ ኪሩቤል ማለት ነው 🟥 ዘፀአት25፣18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 20 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ። 🔷 ያው ኪሩብ ኪሩቤል ማለት ነው የመላእክት ስም ነው ጌታ እራሱ ለሙሴ እያዘዘው ነው ከታቦቱ ጋር የ መላእክት ምስል እንዲሰራ 🔷🔷🔷 በተጨማሪም🔷🔷🔷
1ኛ ነገስት6፣23 በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ።
29 በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ።
ህዝቅኤል4፣1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት፥
🟥🟥🟥🟥 ያው ከመፅሀፍ ቅዱስ እናሳይ ተብሎ እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ ብቻ የሚል አስተምሮ እራሱ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም 🔷 ማስረጃውም ራሱ መፅሀፍ ቅዱስ ነው👇🏾 🟩2ጢሞ 3፣16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
🟩2ኛ ተሰሎንቄ 2፣15 እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ። 🟩2 ወንድሞች ሆይ፥ በሁሉ ስለምታስቡኝና አሳልፌ እንደ ሰጠኋችሁ ወግን ፈጽማችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። 🟥🟥 ወግ ወይም ቱፊት ደግሞ የሚተላለፈው ከአባት ወደ ልጅ ከትውልድም ወደ ትውልድ ነው 🔷🔷ስለዚህም ነው ነባር የሚባሉት ክርስትናዎች (ካቶሊክ እና ኦርቶዶክስ) ስእል የሚጠቀሙት 🔷 ለምሳሌ በታሪክ (በወግ) የእናትና ልጁን ስእለ አድኖ ሀዋርያው ቅዱስ ሉቃስ እንደሳለው ይታወቃል
🟩🟩 ጣኦቶች እና ስእሎች ከጥንት በአህዛብ የሚመለኩ እስራኤላውያንም እግዚአብሄርን የሚያስቆጣ ጣኦት ይሰራሉ እግዚአብሄርም ይቆጣ ነበር👇🏾
🔷ዘፀአት 32፣4 ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፡— እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው፡ አላቸው።
🟩🟩 ስለነዚህም ስለሚያመልኩአቸው ጣኦቶች እግዚአብሄር እንዲህ ይላል👇🏾
🟥ዘፀአት 20፣በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
🔸🔸 የሐዋርያት ሥራ 17
29፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
👆🏻ይቺን ጥቅስም ለክርስትያኖች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ አድርገው ይጠቀሙባታል ይህ ግን የተፃፈው ለማን እንደሆነ ለማወቅ ከፍ ብሎ ማየት ነው 👇🏼👇🏼
የሐዋርያት ሥራ 17
16፤ ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።
ይሄ የተፃፈው አምላካቸውን ለማያውቁ ጣኦት አምላኪዎች ነው እሱንም አምላክ ብለው ለያዙት ነው
🟩🟩🟩 ምስኪን እና አለማወቃቸውን የማያውቁ ወገኖቻችን ግይ ይህን እግዚአብሄርን ለሚያስቆጡ እና ለሚመለኩ ጣኦቶች እንዳያመልኩ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ እግዚአብሄር እራሱ ላዘዘውና ነብያት እንዲሁም ሀዋርያት ለሰሩት በመፅሀፍ ቅዱስና በቱፊት ማስረጃ ላላቸው ስእለ አድኖ ማስጠንቀቂያ ይጠቀሙበታል
ይህም ችግር መፅሀፍ ቅዱስን ካለማወቅና 1ጥቅስ ብቻ ከመያዝ የሚመጣ ነው ያለዚያማ እግዚአብሄርን ራሱ የሚጋጅ ነገር ይናገራል ብሎም ውሸታም እንደማድረግ ነው
🔷ለምሳሌ 👉🏼 ዘፀአት20፣4-5 እግዚአብሄር ምንም አይነት ምስል እንዳይስል እንዳይቀርፅ ለራሱም እንዳያደርግ ይናገራል እዛው👉🏼 ዘፀአት 25፣18-20 ደግሞ የመላእክቱን ኪሩቤል ምስል እንዳቀርፅ ያዝዛል
🟩🟩 ይህን ቃል በደፈናው የመፅሀፍ ቅዱስ ግጭት የማመስል ነገር ግን መፅሀፍን ካለማወቅና ልክ ከላይ እንደፃፍኩት የቱ እንደተከለከለና የቱ እንደታዘዘ ካለማወቅ የሚመጣ የአእምሮ ግጭት ነው
🔷🔷🔷 ያው ጥቂቱን ነው የነገርኩሽ ከማውቀው በጎደለው ጌታ ኢየሱስ ይሙላበት ከነገርኩሽ ግን ግር ያለሽ ነገር ካለ ጠይቂኝ
ስለ ስእለ አድኖ ግልፅ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ጥያቄሽ እንግባ🙏🏽 🟩በ ኤርሚያስ የተሰጠ ምላሽ🟩 👉🏼ለ ጥያቂ እና አስተያየት @ermi_hd
🔶ለቅዱሳን መዘመር ተገቢ ነውን? 🔸🔸መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል??
ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ 🔶(መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡
ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?
ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ🔸 ‹‹መዝሙረ ዳዊት 48
12፤ ጽዮንን ክበቡአት፥
በዙሪያዋም ተመላለሱ፥
ግንቦችዋንም ቍጠሩ፤ ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ 🔸‹‹መዝሙረ ዳዊት 129
5፤ ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡
ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ
👆🏻👆🏻👆🏻👆🏻👆🏻👆🏻👆🏻
🟥ሮሜ 8፣34 ኢየሱስ አማላጅ ነው አይልም ከመፅሀፍ ቅዱስ የማያወላዳ መልስ ከ @ermi_hd
🟥1 መንፈስ ቅዱስ
🟥2ከ መናፍስት ጋር የምናደርገው ውግያ በስጋ ያልሆነ ነው ለዚም👇🏼
ወደ ኤፌሶን 6
12፤ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
13፤ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።
14-15፤ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
16፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
17፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። 👉🏼ስለዚህ መንፈሳዊ ውግያ ነው ሰይጣንን እና የሱን መልእክተኞች የምንዋጋበት መሳርያ ነው ከሱም አንዱ ትልቁን ሰይጣን የምንዋጋበት መሳርያ ፆምና ፀሎት ነው 🔸 ማቴ17
21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፡ አላቸው። ውጤቱ ደግሞ ያው እግዚአቤሄርን መስለን ከጌታ ጋር መኖር እንዳለብን ማወቅና በመጨረሻም መንግስቱን መውረስ ነው 🔶 ማቴ25
34፤ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። 🟥3ኛ ጥያቄ ግን አሜን ነው ሚባለው😁 ጥያቄ ሳይሆን ቀጥታ የእግዚአብሄርን ቃል ነው የተጠቀሰው 🔶ማቴ5
9፤የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥
የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ምን ለማለት እንደፈለገም ግልፅ ነው ከእግዚአብሄር የተወለደ ክርሽስትያን በስራው የአባቱ ልጅ እንደሆነ የሚገልጥበት አንዱ መንገድ ማስታረቅ ነው።🙏🏾
История названий канала
14.08.2026
название
-1001382126493
→
Orthodox
Дата — момент, когда изменение заметил наш обход.