Ru
Главная → Каналы → Другое → ግጥም ፍቅር ቅኔ

ግጥም ፍቅር ቅኔ

@hollypoem · Другое
2 280подписчиков сейчас
Подписаться в Telegram

Публикации всего: 74

Постов на странице: 10 30 50 Страница 1 из 8
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ: በየቦታው እየተካሄደ ያለ አንድ ገራሚ የማስመሰል ትዕይንት አለ። በኢንተርኔት ላይ፣ በሰዎች ጭውውት ውስጥ፣ ሰዎች ሳያስቡ በሚደጋግሙት ምክር ውስጥ ታዩታላችሁ። ሁሉም ሰው ደስተኛ መስሎ ለመታየት ይሞክራል—ወይም ቢያንስ ወደ ደስታ የቀረበ ለመምሰል። ፈገግታ የሞላባቸው ፎቶዎች። የሚያነቃቁ ጽሑፎች። ስለ "ብርታት”፣ “አዎንታዊ አስተሳሰብ” እና “ምርጥ ሕይወት ስለመኖር” የማያቋርጡ ወሬዎች። ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ የሆነ የማይመች ስሜት ይጀምራቹሃል። እንደ ሀዘን ሳይሆን ጥርጣሬ!! ምክንያቱም በውስጣቹህ ከዚህ ሁሉ ነገር ጀርባ የሆነ አርቴፊሻል (የውሸት) ነገር እንዳለ ግማሹ እኔነታችሁ ያውቀዋል። ሰዎች ፈጽሞ ደስታ አይሰማቸውም ማለት አይደለም። በእርግጥ ይሰማቸዋል። እውነተኛ የደስታ ጊዜያት አሉ። እውነተኛ ሳቅ። እውነተኛ ግንኙነት። ጥሩ ጭውውት። ስክን፣ ረጋ ያለ ጠዋት። ውስጣችንን ጠልቆ የሚነካ ሙዚቃ። ከችግር በኋላ የሚመጣ እፎይታ። ፍቅር። ጓደኝነት። እረፍት። እነዚህ ነገሮች አሉ። ግን ዘመናዊው ሕይወት ሊሸጥልን የሚሞክረው የደስታ ምስል ሙሉ በሙሉ የተለየ ነገር ነው። ቅጽበት አይደለም። ሁኔታ ነው። ደስታ ቋሚ ስሜታዊ ጸባያችን መሆን ያለበት አይነት ሁኔታ ነው። የተሳካ ሕይወት ማለት ችግር የጠፋበት ሕይወት እንደሆነ አይነት። እናም ችግሩ የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው። ምክንያቱም ማንም የሰው ልጅ በእውነቱ እንደዚያ አይኖርም። አንዳንድ ቀናት በተስፋ ተሞልታችሁ ትነቃላችሁ። ሌሎች ቀናት ደግሞ ያለ ምንም ግልጽ ምክንያት ባዶነት ይሰማቹሃል። አንዳንድ ጊዜ ጠዋት ላይ የሆነ ተነሳሽነት ይሰማችሁና ማታ ላይ ጠፍቶባችሁ ታመሻላችሁ። አንዳንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ነገር አሳክታችሁ እንኳን በሚገርም ሁኔታ እርካታ ታጣላችሁ። የስሜት ዓለማችን ያለማቋረጥ ይለዋወጣል። ችግር ስላለብን አይደለም። የስሜት ሁኔታዎች በተፈጥሯቸው ያልተረጋጉ ስለሆኑ ነው። ይሁን እንጂ በዘመናዊው ባህል አለመረጋጋት እንደ ውድቀት ይቆጠራል። ሁልጊዜ ደስተኛ፣ የተረጋጋ፣ ተነሳሽነት ያለው፣ አምራች እና አመስጋኝ ካልሆናችሁ የሆነ ችግር አለባችሁ ማለት ነው። ስለዚህ ሰዎች ጤናማነትን እንዴት ማስመሰል እንዳለባቸው ይማራሉ። በየቦታው ታዩታላችሁ። ሰዎች ዝምታን ስለሚፈሩ በግድ ጥሩ ነገር ለማውራት ይሞክራሉ። እያንዳንዱን ትግል ገና በደንብ ሳይረዱት ወደ አነቃቂ ንግግር ይቀይሩታል። በውስጥ ታክተው እና ዝለው በአደባባይ ፈገግ ይላሉ። እርግጠኛ አለመሆን አሳፋሪ ስለሚመስል፣ የውስጥ ሰላም እንዳላቸው ያስመስላሉ። እናም ቀስ በቀስ፣ ደስታ ራሱ የውሸት ስሜት መምሰል ይጀምራል። ለዘለዓለም እንዲቆይ ያልተፈጠረን ስሜታዊ ሁኔታ ጠብቆ ለማቆየት መሞከር በጣም አድካሚ የሆነ ነገር አለው። ሕይወታችሁን ሙሉ ፊታችሁ ላይ አንድ ዓይነት ገጽታ ብቻ ይዛችሁ ለመቆየት መሞከርን አስቡት። ውሎ አድሮ፣ ከተፈጥሮ ውጪ ይሆናል። ህመም ሁሉ ይሆናል። ደስታ ተሞክሮ መሆኑ አብቅቶ ግዴታ (የሚጠበቅ ነገር) ሲሆን የሚፈጠረው ይሄው ነው። ስሜቶቻችሁን መቆጣጠር (መጠበቅ) ትጀምራላችሁ። ሀዘን ብቅ ባለበት ቅጽበት፣ ልታጠፉት ትሞክራላችሁ። መሰላቸት ሲመጣ፣ ራሳችሁን አዘናግታችሁ ለመላቀቅ ትጥራላችሁ። ጭንቀት ሲፈጠር ትደናገጣላችሁ—በጭንቀቱ ምክንያት ብቻ ሳይሆን፣ መጨነቅ የለብኝም ብለን ስለምናስብም ጭምር ነው። ግን ምናልባት ችግሩ መጥፎ ስሜቶች መኖራቸው ላይሆን ይችላል። ምናልባት ችግሩ ሊኖሩ አይገባም ብሎ ማመኑ ላይ ይሆናል። ከረጅም ዘመናት በፊት ኤፒኩረስ የተባለ ፈላስፋ ነበረ፤ ብዙ ጊዜ በደስታ (በስጋዊ እርካታ) ያበደ ሰው ተደርጎ በተሳሳተ መንገድ የሚተረጎም ፈላስፋ ነው።  ግን በጥልቀት ስትመለከቱት፣ እሱ በእርግጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከዚህ እርካታ በጣም የረጋ ነገርን ነበር። ማለቂያ የሌለው ደስታ (እርካታ) አልነበረም። የስሜት መነቃቃት አልነበረም። ቀላልነትን ነበር። አላስፈላጊ ከሆነ ሥነ-ልቦናዊ ትርምስ ነጻ የሆነ ሕይወት። ከጓደኞች ጋር የምትጋሩት ትንሽ ምሳ። የተረጋጋ አእምሮ። ከማያቋርጥ መሻት (ምኞት) ነጻ መሆን። ይህ ዘመናዊው ዓለም ለደስታ ካለው ከልክ ያለፈ አባዜ በጣም የራቀ ይመስለኛል። ዛሬ፣ ደስታ በውስጣችሁ ያለማቋረጥ ማምረት ያለባችሁ ምርት ተደርጎ ነው የሚታየው። እርካታ ሊሰማችሁ ይገባል። ተነሳሽነት ማሳየት አለባችሁ። Passionate መሆን አለባችሁ። እርግጠኛ መሆን አለባችሁ። ይህ ካልሆነ ደግሞ፣ ራስ-አገዙ ባህል ሊያርማችሁ ከተፍ ይላል። በደንብ አሰላስል (Meditate አድርጉ)፣ positive ነገር አስቡ፣ mindሴትህን አስተካክል፣ የተሻለ energy ወደራሳችሁ ሳቡ (manifest አድርግ) ይሏቹሃል። የስሜት መወሳሰብ ማለት ልክ ራስን በአግባቡ ማስተዳደር አለመቻል እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል። ግን ሕይወት እንደዚያ በተስተካከለ መንገድ አትጓዝም። ንቃተ-ህሊና ራሱ ያልተረጋጋ ነው። ስሜቶቻችን ለትዝታ፣ ለእርግጠኛ አለመሆን፣ ለፍርሃት፣ ለፍላጎት፣ ለድካም፣ ለብቸኝነት፣ ለሥነ-ህይወት፣ እና ለጊዜ ምላሽ ይሰጣሉ። ስሜቶቻችን የሚለዋወጡት በህይወት ስላለን ነው። ሲጀመርም አላፊ በሆነ ህልውና ውስጥ ቋሚ የስሜት ሁኔታ እንዲኖር መጠበቅ ፈጽሞ እውነታውን ያገናዘበ አይደለም። እና በእውነቱ አንዳንድ የሀዘን አይነቶች ችግሮች እንኳን አይደሉም። ግልጽነት (ነገሮችን አጥርቶ የማየት ውጤት) ናቸው። ስጋት ውስጥ መሆን ትክክለኛው ምላሽ የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ። ሕይወታችሁን በጥልቀት ስትመለከቱና እርግጠኛ እንዳልሆናችሁ ስትገነዘቡ። በዙሪያችሁ ካሉ ሰዎች ጋር መራራቅ ሲሰማችሁ። የወደፊቱ ጊዜ ግልጽ ያልሆነ ሲመስላችሁ። ሕይወት ምን ያህል አሰልቺና ተደጋጋሚ እንደምትሆን ስትረዱ። ስለነዚህ ነገሮች ያለን ግንዛቤ ለምን በአዎንታዊነት ይዋጣሉ? አንዳንድ ጊዜ የውሸት ደስታ ተስፈኝነት አይደለም። ከእውነታው መሸሽ ነው። ሰዎችም ልዩነቱ ሊሰማቸው ይችላል። አንዳንድ የአዎንታዊነት አይነቶች ስትሰሟቸው ባዶ ሆነው የሚሰሟችሁ ለዚህ ነው። ምክንያቱም እውነታውን በፍጥነት ዘለው ያልፋሉ። ምንም ነገር ሳይረዱ ለመጽናናት ይጣደፋሉ። ስሜትን ማዳመጥ እንዳለባችሁ ነገር ሳይሆን መቆጣጠር እንዳለባችሁ ነገር አድርገው ይቆጥሩታል። ይህ ማለት ስቃይ ከደስታ ይበልጣል ማለት አይደለም። ጨለምተኛ ወይም ስሜት አልባ መሆን አለብን ማለትም አይደለም። ዋናው ሀሳብ ደስታን መቃወም ሳይሆን ደስታን ማምለክ ማቆም ነው። ምክንያቱም ደስታ የሕይወት ዋና ግብ ሲሆን፣ እውነታውን በሐቀኝነት መጋፈጥ አትችሉም። እያንዳንዱን ተሞክሯችሁን በስሜት መመዘን ትጀምራላችሁ። "ይሄ ደስተኛ ያደርገኛል?" "አሁን ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው?" "በሕይወቴ በቂ ደስታ እያገኘሁ ነው?" እናም መልሱ አይደለም ከሆነ ድንጋጤ ይጀምራል። ግን ምናልባት ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት የሚሰጥ ሕይወት ላይሆን ይችላል። ምናልባት ነገሮችን በግልጽ የሚያይ ሕይወት ሊሆን ይችላል። ግልጽነት ከደስታ የተለየ ነው። ግልጽነት ምቾት ማጣትን ሊያካትት ይችላል። እርግጠኛ አለመሆንን ሊያካትት ይችላል። ስለራሳችሁ እና ስለ ዓለም ከባድ እውነቶችን መጋፈጥን ሊያካትት ይችላል። ግን እውነተኛ ነው። እና ፍጹም ባይሆንም እንኳ፣ እውነታው ላይ መቆም በሚያስገርም ሁኔታ የሚያረጋጋ ነገር አለው። ~ ደስታና የዘመናዊው ዓለም ልክፍት ✍️ዮናታን በጋሻው @hollypoem
👍 2 ❤ 1 Перейти к публикации →
ጦርነት! (አሌክስ አብርሃም) ሳይጀመር...​ ዛቻው፣ ማስፈራሪያው፣ ቅስቀሳው፣ ፍርሃትና ስጋቱ፣ ጥላቻው መንፈስህን ይገድለዋል፤ ቀንህንና ጊዜህን ይቀማሃል። ጦርነቱ ይጀመራል...ሰላምህን ይነጥቅሃል፣ ደህንነትና የህግ ዋስትናህን ይነጥቅሃል፣ የምትወዳቸውን ሰዎች ይነጥቅሃል፤ ንብረትህን ይነጥቅሃል፤ ልማትህን፣ ተስፋህን፣ መተማመንህን፣ አካልህን፣ ዕድሜህንና ሕይወትህን ጭምር ይነጥቅሃል። በደም ያጨቀይሃል። ​ከቆመ በኋላ....ክፍለ ዘመን ወደኋላ ወስዶ ያቆመሃል።  "ይመለስ ይሆን?" የሚል ስጋት ያሸክምሃል፤ በርጋጊ ትሆናለህ፣ ትዝታው ዕድሜ ልክህን ያስቃዠሃል፤ የእድሜ ልክ የጥላቻና የሰቆቃ ታሪክ ያወርስሃል። ይሙቱ ይዳኑ የማታውቃቸው ልጆችህ፣ ወንድሞችህ፣ ጓደኞችህ ሞቱም ዳኑም ሳይባል ይጠፋሉ፤ ጠባቂ ልብ ታቅፈህ ትቀራለህ። የፈረሰ ከተማ ፣ የፈራረሰ ሰብዓዊነት፣ የፈራረሰ ፍቅር ፣ትሸከማለህ፤ የፈራረሰ እምነት ትሸከማለህ። ቂም በቀል ታረግዛለህ። ​ጦርነት ሳይጀመርም፣ ተጀምሮም፣ አቁሞም ሰቆቃ የሆነ የማይፀዳ የሕይወት ጥቀርሻ ነው። አትጀምረው፤ ከጀመርከው ለማቆም የመጨረሻ አቋምህን ተጠቀም፤ ከቆመ ደም የበከላት ምድርህን ተባብረህ አፅዳ። @hollypoem
❤ 1 Перейти к публикации →
ያ ጊዜ የምንለው መስከር'ም በቃኝ ሲል ጥቅምት ሲገባ እናያለን ሁሌም ህዳር የሚያፈራ ሌላ ውብ አበባ የእኔ ጥያቄ ግን? ሰላም የሀገሬን ጡት                 መቼ ነው የሚጠባ? By ይክበር ፀጋዬ @hollypoem
🔥 1 Перейти к публикации →
ይለቀሳል በሐዘን ፥ ባይኖርም አባባይ ዕንባም አይገደውም ፥ ይወርዳል እንደ አባይ ደስታ ግን ሰው ይሻል አብሮ የሚያሳስቀው ፥ አጃቢ ተከታይ ሲዳር ሚዜ ሚሆን ፥  ሲዘፍን ተቀባይ ። ሰው በደስታ ድሎት ቦታ አልበቃ ብሎት ሲሆን ሐሴት ባሴት ከአጀብ ተነጥሎ ፥ ተደብቆ በሌት መች ያቅታል ማዘን ፥ በሲቃ ማቃሰት ? ይልቅ የሚከብደው ፥ ለብቻ መደሰት ። By Habtamu Hadera @hollypoem
👍 1 Перейти к публикации →
#አንዲት_ቃል ስጋር ሆኖ ሳለ          የሌት ተቀን ውሎ አምላክም ይሰጣል           ማረፊያ እንካ ብሎ ለቅዱስ ሚካኤል አማላጅን ብልክ ጠይቄ ስለሷ ሶስት ወር  አስቆጥሮ                  ተዋኀደኝ ነብሷ ፀሎት ሰመረና ሽምጥ ያጋለብኩት የህይወት ዘመኔ ባንዲት ቃል አበቃ አንቺን ሰጦ ለኔ አንቺ ጋ ስቀመጥ ለእልፍ አእላፉ የሚለፈልፈው ተዘጋ ምላሴ ብክን ክን ክን ሚለው ተረጋጋ ነብሴ እውክታ የሞላው ኑሮዬ እና ቀኔን እረሳሁት ታግዬ ታግዬ ውሎዬን አረፍኩት እ ር ፍ ዮኒ      ኣታን yonatoz @hollypoem
❤ 1 👍 1 Перейти к публикации →
በቃኝ ----------------------- እሳት ሆኘ ስነድ፥ አንች ቆፈን ወርሶሽ ሎሚ ብወረውር፥ እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ ዝምድና ሳያንሰን፥ እየቆየሽ ባዳ መላመድ ሳይጎድለን፥ እያደርሽ እንግዳ፤ እንግዲህ ደህና ሁኝ! ምኞቴም በረደ፥ ቁጣየም አለፈ ከእድሉ ጋር ታግሎ፥ ማነው-ያሸነፈ። By Bewuketu Siyum @hollypoem
❤ 3 👍 1 Перейти к публикации →
°. ልቤን አታናጋው እንደቆየ ተስፋ፣ ሳልፈልግህ መጥተህ ስወድህ አትጥፋ። By መክሊት @hollypoem
👍 2 Перейти к публикации →
ትንቢት አይደለም! (አሌክስ አብርሃም) በዚህ ሳምንት ሁለት ቲክቶከሮች ራሳቸውን ማጥ*ታቸውን አነበብኩ። ሁለቱም ወጣቶች። ይህ የተለየ የነብይነት ጸጋ የሚጠይቅም ነገር አይደለም። ነገር ግን በተለይ ቲክቶክ ላይ የምናያቸው ልጆች፣ የብዙዎቹ መጨረሻ አያምርም። ራስን ማ*ጥፋት፣ የአእምሮ መታወክና የመሳሰሉት ችግሮች ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል። ለምን? ​የመጀመሪያው ጉዳይ፦ ዓለም አቀፍ የቢዝነስና የማርኬቲንግ ኤክስፐርቶች ባወሳሰቡት ዘግናኝ ሲስተም ውስጥ፣ ድክም ያለ ኢትዮጵያዊ ስነ-ልቦናና ዕውቀት ይዘው ነው የሚገቡት። ሳንቲሙ ብቻ ነው የሚታያቸው። ላይኩ ትንንሽ እውቅናው ያጓጓል። ሲስተሙ  ልክ እንደ አምልኮ ሙሉ ለሙሉ መሰጠትና የራስን ማንነት መጣል ይጠይቃል። የማሰቢያ ይቅርና የመተንፈሻ ጊዜ አይሰጥም። ከራስ ጋር፣ ካደጉበት ባህልና እምነት ጋር በየቀኑ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ሕዝቡ ደግሞ ራሱን ጨዋ አድርጎ እየሳለ፣ ብልግናውን እንደ ሱቅ አሻንጉሊት አልብሶ የሚያቆማቸው ሚስኪን ወጣቶች በጭብጨባ በጊፍት ይፈጥራል። በፈለገው ልክ ይሰድባቸዋል፤ ያንቋሽሻቸዋል። ለሚያገኟት ሳንቲም ሲሉ ይህን ሁሉ ይሸከማሉ። ይህ ደግሞ መጨረሻው ባዶነት ነው። ​ሁለተኛው፦ የማይሞላው የሲስተሙ የብልግና ፍላጎት ነው። ዛሬ አንዲት ሴት ጫማዋን ብታወልቅና ሰዎች እግሯን ቢያደንቁ፣ ነገ ቀሚሷን እንድታወልቅ ይገፋፋታል። ከነገ ወዲያ... ራቁቷን ካስቀራት በኋላ እንደ ቆሻሻ ይጥላታል። ከዚያ በኋላ "እዩኝ እዩኝ" ለማለት የማይደረግ ነገር የለም። ለምናችሁ ፊቷን ያያችኋት ልጅ ለምናችሁ ርቃኗን ትቆማለች። መቸ ባገኘናቸው ብለን የጓጓንላቸው  ታዋቂ ሰዎች ሳይቀሩ ዘግናኝ ውድቀት ሲወድቁና እንደውሻ ሂዱ ወደዚያ እየተባሉ ሲንቋሸሹ  ተመልክተናል። ዛሬ ብሩም ክብሩም እጃቸው ላይ የለም፤ እንደአእምሮ ህመምተኛ ድሪቶ ሐሳብ እየጎተቱ በየድጅታል ሙዚቃ ቤቱ በር እየደነሱ ነው። ልክ እንደ ቁማር ነው ሲስተሙ፣ ትንሽ ተስፋ ይሰጠሀል ያለህን ይቀመሃል። ​ሶስተኛው፦ ለትምህርትና ለሌላ ሥራ ያለውን ፍላጎት መግደሉ ነው። ዛሬ ላይ ቀላል የማይባል ሕዝብ በዩቲዩብና በቲክቶክ ምክንያት ለሥራም፣ ለትምህርትም ሆነ ለማህበራዊ ኑሮ ያለው ፍላጎት እየሞተ ነው። ነገ ከነገ ወዲያ፣ በተለይ ድሃ አገራት የነፃ ኢንተርኔት እንዲያገኙ መደረጉ አይቀርም። ያኔ አሁን ከምናየው በብዙ ሺህ እጥፍ የሚበልጥ "ጉድ" አደባባይ ይወጣል። እንደ ኢትዮጵያ አይነት ከባድ ድህነትና የደከመ ዓለም አቀፍ ዕውቀት ያለባቸው አገራት፣ ውስብስቡን የስነ-ልቦና ወጥመድ ቀርቶ የዕለት ተዕለት ድርጊቱንም መረዳት ዳገት ይሆንባቸዋል። ሌላውን ተውት ብዙወች  የተሟላ እንቅልፍ እንኳን አይተኙም። የብዙወቻችን ሲስተም ተዛብቷል። ​አራተኛ፦ የውሸት ሀብትና ሀብታሞች ይፈጠራሉ። አይሰሩም፣ አያሰሩም፣ አዲስ ነገርም አይፈጥሩም፤ ግን ብር እጃቸው ላይ ስለሚገባ የበለጠ ገንዘብ ለመስራት ሲስተሙን ይረብሹታል። ሴተኛ አዳሪነት፣ ሱስ፣ አደገኛ መጤ ባህሎች ፣ ብልጭልጭ ነገር  በተለያየ ሽፋን ባህል ይሆናል። የሶሻል ሚዲያው ስብከት የቆምንበትን ማንነት ያፈራርሰዋል። በመጨረሻም ማንም ምንም አይኖረውም። እርሻ አታዩም ፋብሪካ የለም ነገር ግን ሐብታም እዛና እዚህ ታያላችሁ። አምስተኛና አሳዛኙ ነገር  የሚሰበከው ከሶሻል ሚዲያ ይገኛል የሚባለው ገንዘብ አለመኖሩ ነው። ጥቂቶች ጥቂት ይከፈላቸዋል፣ ሌላው  ሕዝብ ግን ራሱን ጭምር ይከፍላል። ጊዜውን፣ ተስፋውን ሕይወቱን ቤተሰቡን! በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ብዙ ወጣቶች ራሳቸውም ላይ ሆነ በሌሎች ላይ ዘግናኝ ነገር ማድረጋቸው አይቀሬ ነው! የተሞከረ የታየ እውነት ነው። ​ምን እናድርግ??? ​እጃችን ላይ ያለውን ሥልጣን እንጠቀም፦ ልጆችን ቢያንስ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (High School) በፊት ከሶሻል ሚዲያ እናርቃቸው። እንደ አገር ሥጋት፣ እንደ ሰውም ክብረ-ቢስነት ውስጥ የሚከቱ ይዘቶችን (Contents) ሪፖርት በማድረግ እናስወግድ። ጥሩ ኮንቴንቶችን እናበረታታ።  የግለሰቦችን ነፃነት የሚጋፉ ስርጭቶች በሙሉ እንደ ሕዝብ ጠላት ሊታዩ ይገባል። ​የሃይማኖት ሰዎች ከዚህ ግፊያና ፍትጊያ ይራቁ፦ ወንጌል ለመስበክ በሚል ሰበብ፣ መተማመንንና አንድነትን ከማስፋፋት ይልቅ ባዶነትን ለትውልድ እያወረሱ ነው። እንደ ተቋም በሥርዓት ከሚሰራጩ አስተምህሮቶች ውጭ፣ በእምነት ስም፣ ባልሰለጠኑና ሞራል በሌላቸው ግለሰቦች  የሚሰራጩ ፀያፍ ነገሮች ሁሉ ሊታገዱ ይገባል። ​ውይይትና ሕግ፦ በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ምሁራንና ሕዝብን ያሳተፈ ውይይት በማድረግ አስፈላጊ ሕጎች ይውጡ። ይህ ማለት መንግሥት ለራሱ ሥልጣን ማራዘሚያ አፋኝ ሕግ ያውጣ ማለት አይደለም። ​እንጸልይ ጓዶች፦ የአሁኑን ድህነትና መመሳቀል የሚያስናፍቅ "የቆሸሸ ጊዜ" ከፊታችን እየመጣ ነው። ጨለምተኝነት አይደለም የእጃችሁን ሰዓት አይታችሁ ምሽቱ ምን ያህል ጊዜ እንደቀረው የመናገር ያህል ቀላልና ግልፅ ነው። @hollypoem
👍 1 Перейти к публикации →
ተኳረፍኩኝ ካገሬ ጋር ተሳቅቄ ሆኜ ከዳር ጀርባየን አላምነውም ጠላቴንም አላውቀውም ማውቀውንም አላውቀውም ባውቀውም አልንቀውም መተንፈሻ አጣ አገሩ ኩፍ በዛ በየዳሩ ሰቀቀን በርዞታል አይጥምም አየሩ ዘር በዛ ባገሩ አዲስ ጠፋች በአበባ ሚሰቴ አሏት ባለቤቴን ቀለበቴን አይቶ አገባ አገሯ ዳር ናት ሰውም ወድቋል ጥጉጥጉ ሬሳው ሳይነሳ ዘሩን ዘሩን እየፈለጉ አዲስ አመት ባክህ ና አታብቅል አበባ ኢትዬጵያን ሚሏት ሀገር ባይሆን ይዘህ ግባ . . ግዕዝ ሙላት geez_mulat
❤ 3 Перейти к публикации →
ትናንትን በዛሬ_! ያቺ ትናንቴ ሀ--ሁ-- ዬ  የነበረች፣ የሆነ ቀን ዛሬ ነበረች።              እንድያው ሳላስብ ዘንግቻት፣              ይሄው ዛሬ አስታወስኳት። ቁጭ ብዬ በዛሬ ፊት ስታዘባት፣ የኳተነች ጎስቋላ ፊት የነበራት፣              በደስታ እና በፈተና የረሳዃት፣               ይሄው አሁን በዛሬ ፊት አነሳዃት። ከፊቴ ፊት ቁጭ ብላ ስትስቅብኝ፣ ስጠብቃት ብን ብላ እንዳጠፋኝ።                ባትሆን ኖሮ የኔ ትናንት፣                 ይችን ዛሬ-- አሁን ባልል ታምኜባት። መምህሬ የኔ ትናንት፣ መቆሚያዬ የዛሬ እናት፣           የጉዞዬ እርሾ የነገዬ ርስት፣           የጉልበቴ ሰደፍ የዘመኔ ሽበት።                                                 በ መ/ር ሰይድ: ነሐሴ 6, 2018
👍 1 Перейти к публикации →
1 2 3 … 7 8

Другие каналы категории